ሐዋርያት ሥራ 11:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ! ይህማ አይሆንም፤ ርኩስ ወይም ያልተቀደሰ ነገር ፈጽሞ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ‘ጌታ ሆይ! አይሆንም፤ ርኩስ ወይም የሚያስጸይፍ ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅምና፤’ አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን ‘አይሆንም ጌታ ሆይ! ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ ነገር በአፌ ገብቶ አያውቅም’ አልኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘አቤቱ፥ ከቶ አይሆንም፤ ንጹሕ ያልሆነ ርኩስ ነገር ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም’ አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ “ጌታ ሆይ፥ አይሆንም፤ ርኵስ ወይም የሚያስጸይፍ ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅምና” አልሁ። |
በጌታ በኢየሱስ ሆኜ በራሱ ንጹሕ ያልሆነ ምንም ምግብ እንደሌለ ተረድቻለሁ፤ ነገር ግን አንድ ሰው አንድን ነገር ንጹሕ እንዳልሆነ የሚቈጥር ከሆነ፣ ያ ነገር ለርሱ ንጹሕ አይደለም።
ያላመነ ባል በሚስቱ ተቀድሷልና፤ ያላመነችም ሚስት በሚያምን ባሏ ተቀድሳለች፤ አለዚያማ ልጆቻችሁ ርኩሳን በሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።