ሐዋርያት ሥራ 10:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታየውም ለሁሉ ሰው ሳይሆን፣ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ዐብረነው ለበላንና ለጠጣን፣ እግዚአብሔርም አስቀድሞ ለመረጠን ለእኛ ለምስክሮቹ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተገለጠውም አስቀድሞ በእግዚአብሔር ለተመረጡት ምስክሮች ነው እንጂ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ እርሱ ከሞት ከተነሣ በኋላ እኛ ከእርሱ ጋር አብረን የበላንና የጠጣን ምስክሮቹ ነን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይኸውም ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን አስቀድሞ ለመረጣቸውና ምስክሮች ለሚሆኑት ብቻ ነው እንጂ፤ የመረጣቸው የተባልንም እኛ ነን፤ ከሙታንም ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን። |
እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም። እናንተ ግን፣ ዐብሯችሁ ስለሚኖርና በውስጣችሁ ስለሚሆን ታውቁታላችሁ።
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።
ይኸውም፣ ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ ተለይቶ እስካረገበት ቀን ድረስ የነበረ መሆን አለበት፤ ምክንያቱም ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ከእኛ ጋራ የትንሣኤው ምስክር እንዲሆን ያስፈልጋል።”
ከእነርሱም ጋራ በማእድ ተቀምጦ ሳለ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “ከኢየሩሳሌም አትውጡ፤ ነገር ግን እኔ ስናገር የሰማችሁትን፣ አብ የሰጠውን ተስፋ ጠብቁ፤