2 ጢሞቴዎስ 4:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖስ፣ ጥቅልል መጻሕፍቱን፣ በተለይም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱን እንዲሁም መጻሕፍቱን በተለይም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስትመጣ በጢሮአዳ በካርፑስ ዘንድ የተውኩትን ካባ ይዘህልኝ ና፤ መጻሕፍቱንም ይልቁንም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖሱንና መጻሕፍቱን ይልቁንም በብራና የተጻፉትን አምጣልኝ። |
ብዙ ጥሬአለሁ፤ ብዙ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ ተርቤአለሁ፤ ተጠምቻለሁ፤ ብዙ ጊዜ ምግብ ሳልቀምስ ኖሬአለሁ፤ በብርድና በዕራቍትነት ተቈራምጃለሁ።