2 ጢሞቴዎስ 4:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእኔ ጋራ ያለው ሉቃስ ብቻ ነው። ማርቆስ በአገልግሎቴ ስለሚረዳኝ ከአንተ ጋራ ይዘኸው ና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስን ከአንተ ጋር ይዘኸው ና፥ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ስለሚጠቅመኝ ፈልገህ ይዘኸው ና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ። ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው። |
ዐብሮኝ የታሰረው አርስጥሮኮስና የበርናባስ የአክስቱ ልጅ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ስለ ማርቆስ መመሪያ ደርሷችኋል፤ እንግዲህ ወደ እናንተ ሲመጣ ተቀበሉት።
እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ከጠቀስኋቸው ነገሮች ቢያነጻ፣ ለክቡር አገልግሎት የሚውል፣ የተቀደሰ፣ ለጌታው የሚጠቅም፣ ለመልካም ሥራም ሁሉ የተሰናዳ ዕቃ ይሆናል።