2 ነገሥት 9:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀብሯት ሲወጡ ግን ከራስ ቅሏ፣ ከእግሯና ከእጇ በቀር ሌላ ያገኙት አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊቀብሩአት የሄዱ ሰዎች ግን ከራስ ቅልዋ፥ ከእግሮችዋና ከእጆችዋ አጥንት በቀር ምንም አላገኙም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊቀብሩአት የሄዱ ሰዎች ግን ከራስ ቅልዋ፥ ከእግሮችዋና ከእጆችዋ አጥንት በቀር ምንም አላገኙም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊቀብሩአትም በሄዱ ጊዜ ከአናቷና ከእግርዋ ተረከዝ ከመዳፍዋም በቀር ምንም አላገኙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊቀብሩአትም በሄዱ ጊዜ ከአናትዋና ከእግርዋ ከመዳፍም በቀር ምንም አላገኙም። |
ተመልሰውም ይህን ሲነግሩት፣ ኢዩ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ለባሪያው ለቴስብያዊው ለኤልያስ፣ በኢይዝራኤል ምድር ዕርሻ ውስጥ ውሾች የኤልዛቤልን ሥጋ ይበሉታል፤
አንድ ሰው መቶ ልጅ ሊኖረውና ብዙ ዓመት ሊኖር ይችላል፤ ምንም ያህል ይኑር፣ በሀብቱ ደስ ካልተሠኘበትና በአግባብ ካልተቀበረ፣ ከርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል እላለሁ፤
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፤ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከዘሩ አይገኝም፤ ሬሳውም ወደ ውጭ ተጥሎ ለቀን ሐሩርና ለሌሊት ቍር ይጋለጣል።