እንግዲህ እግዚአብሔር በርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፣ ንቃሃለች፤ ታቃልልሃለችም፤ የኢየሩሳሌም ልጅ፣ አንተ ስትሸሽ ራሷን ነቅንቃብሃለች።
2 ነገሥት 19:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕዝቅያስ ሆይ፤ ምልክቱ ይህ ነው፤ “በዚህ ዓመት በገዛ እጁ የበቀለውን፣ በሚመጣው ዓመት ደግሞ የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፥ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የሚበቅለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፥ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የሚበቅለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህም ለአንተ ምልክት ይሆንልሃል፤ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላለህ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራለህ፤ ታጭድማለህ፥ ወይንም ትተክላለህ፤ ፍሬውንም ትበላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “‘ይህም ምልክት ይሆንሃል፤ በዚህ ዓመት የገቦውን፥ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ፤ ታጭዱማላችሁ፤ ወይንንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ። |
እንግዲህ እግዚአብሔር በርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፣ ንቃሃለች፤ ታቃልልሃለችም፤ የኢየሩሳሌም ልጅ፣ አንተ ስትሸሽ ራሷን ነቅንቃብሃለች።
እግዚአብሔርም፣ “እኔ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ እኔ የላክሁህ ለመሆኑ ምልክቱ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብጽ ካወጣሃቸው በኋላ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።
“ሕዝቅያስ ሆይ፤ ይህ ምልክት ይሆንልሃል፤ “በዚህ ዓመት የገቦውን፣ በሚቀጥለው ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
ነገር ግን ለይሁዳ ቤት እራራለሁ፤ በቀስት ወይም በሰይፍ ወይም በጦርነት ወይም በፈረሶችና በፈረሰኞች ሳይሆን በአምላካቸው በእግዚአብሔር አድናቸዋለሁ።”
ምድሪቱም በሰንበት ጊዜዋ የምታስገኘው ማንኛውም ፍሬ ለአንተ፣ ለወንድ ባሪያህ፣ ለሴት ባሪያህ፣ ለቅጥር ሠራተኛህና ከአንተ ጋራ ለሚኖር መጻተኛ ምግብ ይሁን፤