ኢየሱስም እንደ ገና እጆቹን በሰውየው ዐይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ዐይኖቹ በሩ፤ ብርሃኑም ተመለሰለት፤ ሁሉንም ነገር አጥርቶ ማየት ቻለ።
2 ቆሮንቶስ 3:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን የፊቱ ማንጸባረቅ እየጠፋ ሲሄድ መጨረሻውን እንዳይመለከቱ፣ ፊቱን በጨርቅ እንደ ሸፈነው እንደ ሙሴ አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኩር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ ፊቱን እንደ ጋረደው እንደ ሙሴ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴ እየከሰመ የሚሄደው የፊቱ መንጸባረቅ እስኪወገድ ድረስ እስራኤላውያን እንዳያዩ ፊቱን ይሸፍን ነበር፤ እኛ ግን እንደ እርሱ አይደለንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያን ይሻር የነበረውን መጨረሻ፥ የእስራኤል ልጆች እንዳያዩት ፊቱን ይሸፍን እንደ ነበረው እንደ ሙሴ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም። |
ኢየሱስም እንደ ገና እጆቹን በሰውየው ዐይኖች ላይ ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ዐይኖቹ በሩ፤ ብርሃኑም ተመለሰለት፤ ሁሉንም ነገር አጥርቶ ማየት ቻለ።
እንግዲህ እስራኤላውያን ከፊቱ ክብር የተነሣ የሙሴን ፊት ትኵር ብለው ማየት እስኪሳናቸው ድረስ፣ ያ ከጊዜ በኋላ የሚያልፈውና በድንጋይ ላይ በፊደል የተቀረጸው የሞት አገልግሎት በክብር ከመጣ፣