2 ቆሮንቶስ 2:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ወንድሜን ቲቶን እዚያ ስላላገኘሁት መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ ተሰናብቻቸው ወደ መቄዶንያ ሄድሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን መንፈሴ ማረፍ አልቻለም፤ ምክንያቱም እዚያ ወንድሜን ቲቶን አላገኘሁትም። ስለዚህ ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወንድሜን ቲቶን ባለማግኘቴ መንፈሴ አላረፈም፤ ስለዚህ እዚያ ያሉትን ክርስቲያኖች ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ሄድኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሜን ቲቶን ስላላገኘሁት ለሰውነቴ ዕረፍት አላገኘሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ ተለይች ወደ መቄዶንያ ሄድሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከእነርሱ ተሰናብቼ ወደ መቄዶንያ ወጣሁ። |
ቲቶ ወደ እናንተ እንዲመጣ ለመንሁት፤ ወንድማችንንም ከርሱ ጋራ ላክሁት። ቲቶ በዘበዛችሁን? ከርሱ ጋራ በአንድ መንፈስ አልተመላለስንምን? አካሄዳችንስ አንድ አልነበረምን?
እኛም የተጽናናነው በዚህ ምክንያት ነው። ከእኛም መጽናናት በተጨማሪ በቲቶ ደስታ እኛም ይበልጥ ደስ ብሎናል፤ ምክንያቱም ሁላችሁም መንፈሱን አሳርፋችኋል።
በእናንተ ላይ ያለኝን ትምክሕት ለርሱ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም። ነገር ግን ስንነግራችሁ የነበረው ሁሉ እውነት እንደ ሆነ፣ እንደዚሁም ስለ እናንተ ለቲቶ በትምክሕት የነገርነው እውነት መሆኑ ተረጋግጧል።
ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፣ እርሱ እናንተን ለማገልገል ዐብሮኝ የሚሠራ ባልደረባዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችንም የሚጠይቅ ቢኖር እነርሱ የአብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።