2 ቆሮንቶስ 13:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ መሆኑ ነው፤ “ነገር ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ስለሚጸና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። “ማንኛውም ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ መቼም ሁሉ ነገር የሚረጋገጠው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እናንተ ስመጣ እነሆ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ነገር ሁሉ፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ የሚጸና አይደለምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል። |
እንዲሁም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች ከፊት ለፊቱ አስቀምጡና፣ ‘እግዚአብሔርንም ንጉሡንም ሰድቧል’ ብለው ይመስክሩበት፤ ከዚያም አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉት።”
ከዚያም ሁለት ምናምንቴ ሰዎች መጥተው ከፊት ለፊቱ ተቀመጡ፤ በሕዝቡም ፊት፣ “ናቡቴ እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድቧል” ብለው መሰከሩበት። ስለዚህ ከከተማዪቱ ውጭ ወስደው በድንጋይ ወግረው ገደሉት።
“ ‘ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው በሞት የሚቀጣው ምስክሮች ሲመሰክሩበት ብቻ ነው፤ ይሁን እንጂ ማንም ሰው በአንድ ምስክር ብቻ በሞት አይቀጣም።
ወደ እናንተ ለመምጣት ስዘጋጅ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ስመጣ በምንም ነገር ሸክም አልሆንባችሁም፤ እኔ እናንተን እንጂ ከእናንተ ምንም አልፈልግምና፤ ደግሞም ወላጆች ለልጆች ገንዘብ ያከማቻሉ እንጂ ልጆች ለወላጆች አያከማቹም።
በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍ ሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ፣ አንድ ምስክር አይበቃም፤ ነገር በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች የምስክር አፍ መረጋገጥ አለበት።