2 ቆሮንቶስ 11:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና ይህን እላለሁ፤ ማንም ሰው እንደ ሞኝ አይቍጠረኝ፤ እናንተም የምትቈጥሩኝ ከሆነ፣ እኔም በጥቂቱ እንድመካ እንደ ሞኝ ተቀበሉኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገና ይህን እላለሁ፥ ማንም ሰው ሞኝ የሆንሁ አይምሰለው፤ እንደ ሞኝ ለሚያስበኝ፥ እኔም በጥቂቱ እንድመካ እንደ ሞኝ ይቀበለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ማንም ሰው እኔ ሞኝ የሆንኩ አይምሰለው” ብዬ እንደገና እናገራለሁ። ሞኝ ብመስላችሁም እንኳ ጥቂት እንድመካ እንደ ሞኝ አድርጋችሁ ቊጠሩኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም እንዲህ እላለሁ፦ ሰነፍ የሚያደርገኝ አይኑር፤ ያውም ብሆን እኔ ጥቂት እመካ ዘንድ እንደ ሰነፍ እንኳ ብሆን ተቀበሉኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ገና እላለሁ፦ ለማንም ሰው ሞኝ የሆንሁ አይምሰለው፤ ያለዚያ ግን እኔ ደግሞ ጥቂት እመካ ዘንድ እንደ ሞኝ እንኳ ሆኜ ተቀበሉኝ። |
በመመካቴ ሞኝ ሆኛለሁ፤ ለዚህም ያበቃችሁኝ እናንተ ናችሁ፤ ስለ እኔ መመስከር የሚገባችሁ እናንተ ነበራችሁ። ደግሞም እኔ ከምንም የማልቈጠር ብሆንም፣ “ታላላቅ ሐዋርያት” ከሚባሉት በምንም አላንስም።
መመካት ብፈልግ እንኳ እንደ ሞኝ መቈጠር የለብኝም፤ ምክንያቱም የምናገረው እውነት ነው። ነገር ግን ማንም ስለ እኔ ከሚያየውና ከሚሰማው በላይ እንዳይገምተኝ ከመመካት እቈጠባለሁ።