1 ጢሞቴዎስ 5:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ፍርድን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ፤ በመጀመሪያ የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም በመጀመሪያ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸው ምክንያት በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሴቶች በመጀመሪያ ለክርስቶስ የገቡትን ቃል በማፍረሳቸውም በራሳቸው ላይ ፍርድን ያመጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፊተኛውንም እምነታቸውን ስለ ናቁ ይፈረድባቸዋል፤ |
በምትሰበሰቡበት ጊዜ ለፍርድ እንዳይሆንባችሁ፣ ማንም የራበው ሰው ቢኖር በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር ደግሞ በምመጣበት ጊዜ እደነግጋለሁ።
ወጣት መበለቶችን ግን እንዲህ ባለው መዝገብ አትጻፋቸው፤ ምክንያቱም ሥጋዊ ፍላጎታቸው ለክርስቶስ በገቡት ቃል ላይ በሚያይልበት ጊዜ ለማግባት ይሻሉና።
በተጨማሪም ሥራ መፍታትንና ከቤት ቤት መዞርን ይለምዳሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን፣ የማይገባውን እየተናገሩ ሐሜተኞችና በሰው ጕዳይም ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ደርሷልና፤ እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?