1 ጴጥሮስ 3:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ “ሕይወትን የሚወድድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕይወትን የሚወድ መልካም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ፥ ምላሱን ከክፉ ይጠብቅ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚለው፦ “ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ማየት የሚፈልግ፥ ምላሱ ክፉ ነገር እንዳይናገር፥ ከንፈሮቹ ተንኰልን እንዳይናገሩ ይከልክል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ መላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኵኦልን ከመናገር ይከልክል፤ |
አሁንም አእምሮዬ በጥበብ እየመራኝ ራሴን በወይን ጠጅ ደስ ለማሠኘት፣ ሞኝነትንም ለመያዝ ሞከርሁ፤ ሰዎች በዐጭር የሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ባለው ላይ ቢሠሩት ሊጠቅማቸው የሚችል ምን እንደ ሆነ ለማየት ፈለግሁ።
ኢየሱስም፣ “ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንዱ ብቻ ነው፤ ወደ ሕይወት ለመግባት ከፈለግህ ግን ትእዛዞቹን ጠብቅ” አለው።
ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ እንጂ እንዲሁ ባዶ ቃሎች አይደሉም፤ በእነርሱ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፣ በምትወርሷትም ምድር ረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”