እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ።
1 ነገሥት 4:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ ቤንሑር፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነዚህም ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችና የሚያስተዳድሩአቸውም ግዛቶች ስም ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፥ ቤንሑር፦ ኰረብታማ የሆነችው የኤፍሬም አገር ገዢ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስማቸውም ይህ ነበረ፤ በተራራማው ሀገር በኤፍሬም የሖር ልጅ ቢዖር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስማቸውም ይህ ነበረ፤ በተራራማው አገር በኤፍሬም የሑር ልጅ፤ |
እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ።
እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት በኰረብታማው የኤፍሬም ምድር የምትገኘውን ተምናሴራ የምትባለውን የፈለጋትን ከተማ ሰጡት፤ እርሱም ከተማዪቱን ሠራ፤ መኖሪያውም አደረጋት።
እንዲሁም የአሮን ልጅ አልዓዛር ሞተ፤ እርሱም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር በሚገኘው ለልጁ ለፊንሐስ በዕጣ በደረሰው በጊብዓ ምድር ተቀበረ።
በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። በዚሁ ጊዜም በኰረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖር አንድ ሌዋዊ ከይሁዳ ምድር ከቤተ ልሔም አንዲቱን ሴት ቁባት አድርጎ ወሰዳት።