1 ነገሥት 2:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከወንድምህ ከአቤሴሎም በሸሸሁ ጊዜ መልካም ነገር አድርገውልኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች ግን በጎ ነገር አድርግላቸው፤ ማእድህን ከሚካፈሉ ሰዎችም ጋራ ዐብረው ይብሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች ቸርነትን አድርግላቸው። በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች መልካም ቸርነት አድርግላቸው፤ በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ። |
የአባቴ ቤት ሁሉ ከንጉሥ ጌታዬ ሞት እንጂ ሌላ የሚገባው አልነበረም፤ አንተ ግን ባሪያህን በማእድህ ከሚካፈሉት ጋራ አስቀመጥኸው፤ ከዚህ በላይ ይደረግልኝ ብዬ ንጉሡን ለመጠየቅ ምን መብት አለኝ?”
አንተ፣ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን ዕረሱለት፣ ምርቱንም አግቡለት። የጌታህ የልጅ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ምን ጊዜም ከማእዴ ይበላል።” በዚያ ጊዜ ሲባ ዐሥራ ዐምስት ወንዶች ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት።
ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።
የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።
ጌታቸው በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው የሚያገኛቸው ባሮች ብፁዓን ናቸው። እውነት እላችኋለሁ፤ ጌታቸውም በዐጭር ይታጠቃል፤ በማእድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያስተናግዳቸዋል።