የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፣ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ እግዚአብሔርን አላስደሰተውም ነበር።
1 ነገሥት 11:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰሎሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡ ስለ ሸፈተ፣ እግዚአብሔር ተቈጣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰሎሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ጌታ ልቡ ስለሸፈተ፥ እግዚአብሔር ተቈጣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ ተገልጦለት ባዕዳን አማልክትን እንዳያመልክ ያዘዘው ቢሆንም እንኳ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፤ ይልቁንም ከእግዚአብሔር እየራቀ ሄደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ተቈጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ጊዜም ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡናውን መልሶአልና እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ቍጣን ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ጊዜም ከተገለጠለት፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳይከተል ካዘዘው ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡን አርቆአልና፥ እግዚአብሔርም ያዘዘውን ነገር አልጠበቀምና እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቈጣ። |
የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፣ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ እግዚአብሔርን አላስደሰተውም ነበር።
ዖዛ በድፍረት ይህን ስላደረገ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀሠፈው፤ እርሱም በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ እዚያው ሞተ።
በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ፤ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደል? እርሱ ጥሩ እንደሚናገር ዐውቃለሁ፤ እንዲያውም አሁን ወደ አንተ እየመጣ ነው፤ በሚያይህም ጊዜ ከልቡ ደስ ይለዋል።
እግዚአብሔር ግን በእናንተ ሰበብ ተቈጥቶኝ ነበርና አልሰማኝም፤ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ይበቃል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ስለዚህ ነገር አታንሣብኝ።
ምክንያቱም እኔን ከመከተል ልጆችህን መልሰው ሌሎችን አማልክት እንዲያመልኩ ስለሚያደርጉና ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቍጣ በላይህ ነድዶ፣ ፈጥኖ ስለሚያጠፋህ ነው።
“ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ፤ እኔን ከመከተል ተመልሷልና፣ ትእዛዜንም አልፈጸመምና።” ሳሙኤልም እጅግ ተጨንቆ፣ ሌሊቱን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።