1 ቆሮንቶስ 2:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን ይህን በመንፈሱ አማካይነት ለእኛ ገልጦልናል። መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእኛ ግን እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። መንፈስ፥ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር፥ ሁሉን ይመረምራልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኛ ግን እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት ምሥጢሩን ገልጦልናል፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ጥልቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ምሥጢር እንኳ ሳይቀር ሁሉን ነገር ይመረምራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእኛም እግዚአብሔር በመንፈሱ ገለጠልን፤ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምሥጢሩን ያውቃልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። |
“ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤ “ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
“በእኔ በኩል፣ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “በአንተም ላይ ያለው መንፈሴ፣ በአፍህ ያኖርሁት ቃሌ ከአፍህ፣ ከልጆችህ አፍ፣ ከዘር ዘሮቻቸውም አፍ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም አይለይም” ይላል እግዚአብሔር።
በዚያ ጊዜ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አድርጎ እንዲህ አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ፤ አባት ሆይ፤ ይህን ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፤ ይህ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኗልና።
የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል። እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ የሚሰማውን ብቻ ይናገራል፤ እንዲሁም ወደ ፊት ስለሚሆነው ይነግራችኋል፤
በውስጡ ካለው ከራሱ መንፈስ በቀር ከሰው መካከል የአንድን ሰው ሐሳብ የሚያውቅ ማን አለ? እንደዚሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር፣ የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚያውቅ ማንም የለም።
አሁን ከሰማይ በተላከ መንፈስ ቅዱስ ወንጌልን ያበሠሩላችሁ ሰዎች የነገሯችሁን ነገር ባወሩላችሁ ጊዜ፣ እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው። መላእክትም እንኳ ሳይቀሩ እነዚህን ነገሮች ይመኛሉ።
እናንተ ግን ከርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በውስጣችሁ ይኖራልና ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልግም፤ ነገር ግን የርሱ ቅባት ስለ ሁሉም ነገር፣ እውነተኛ የሆነውን እና ሐሰት ያልሆነው እናንተን እንደሚያስተምር፣ እናንተንም እንዳስተማራችሁ በርሱ ኑሩ።
ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለባሮቹ እንዲያሳይ፣ እግዚአብሔር ለርሱ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው፤ ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ ገለጠለት፤
ትምህርቷን ላልተከተላችሁና የሰይጣንም ጥልቅ ምስጢር ነው የሚባለውን ላልተቀበላችሁ፣ በትያጥሮን ለቀራችሁት ለእናንተ ግን ይህን እላለሁ፤ በእናንተ ላይ ተጨማሪ ሸክም አልጭንባችሁም፤