እኔ ሰውን ሁሉ በማንኛውም ረገድ ለማስደሰት እንደምጥር እናንተም እንዲሁ አድርጉ፤ ብዙዎችም ይድኑ ዘንድ፣ ለራሴ የሚጠቅመውን ሳይሆን ለእነርሱ የሚጠቅመውን እሻለሁና።
1 ቆሮንቶስ 11:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምከተል እናንተም የእኔን ተከተሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ክርስቶስን እንደምመስለው እኔን ምሰሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ። |
እኔ ሰውን ሁሉ በማንኛውም ረገድ ለማስደሰት እንደምጥር እናንተም እንዲሁ አድርጉ፤ ብዙዎችም ይድኑ ዘንድ፣ ለራሴ የሚጠቅመውን ሳይሆን ለእነርሱ የሚጠቅመውን እሻለሁና።