ዘካርያስ 8:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስ በርሳችሁ ለመጐዳዳት አንዱ በሌላው ላይ ተንኰል አያስብ፤ በሐሰት አትማሉ፤ እኔ ይህን ሁሉ እጠላለሁ” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባልንጀራችሁ ላይ ክፋትን በልባችሁ አታውጠንጥኑ፤ በሐሰት መማልን አትውደዱ፤ እነዚህን ሁሉ እጸየፋለሁ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዱ በሌላው ላይ ክፉን ነገር በልቡ አያስብ፤ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፤ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል የጌታ ቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፣ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፣ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችሁም በባልንጀራችሁ ላይ ክፉን ነገር በልባችሁ አታስቡ፥ የሐሰትንም መሐላ አትውደዱ፥ ይህን ነገር ሁሉ እጠላለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?
በመካከላችሁ የሚኖሩትን ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ አባትና እናት የሌላቸውን ድኻ አደጎች፥ መጻተኞችንና ችግረኞችን አትጨቊኑ፤ እርስ በርሳችሁ አንዳችሁ ሌላውን ለመጒዳት አታስቡ።’
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።