ዳዊት የዐሞናውያን አምላክ ከሆነው ሚልኮም ተብሎ ከሚጠራው ጣዖት ራስ ላይ ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በውስጡም የከበረ ዕንቊ ያለበትን ዘውድ ወስዶ በራሱ ላይ ደፋው፤ እንዲሁም ከከተማይቱ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤
ዘካርያስ 6:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ከሰጡት ብርና ወርቅ ዘውድ ሠርተህ በሊቀ ካህናቱ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወርቁንና ብሩን ወስደህ አክሊል ሥራ፤ በኢዮሴዴቅ ልጅ በሊቀ ካህኑ በኢያሱ ራስ ላይም አድርገው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርንና ወርቅን ከእነርሱ ውሰድ፥ አክሊሎችንም ሥራ፤ በሊቀ ካህኑ በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋቸው፤ እንዲህም በለው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርንና ወርቅን ከእነርሱ ውሰድ፥ አክሊሎችንም ሥራ፣ በታላቁም ካህን በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋቸው፥ እንዲህም በለው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርንና ወርቅን ከእነርሱ ውሰድ፥ አክሊሎችንም ሥራ፥ በታላቁም ካህን በኢዮሴዴቅ ልጅ በኢያሱ ራስ ላይ ድፋቸው፥ እንዲህም በለው፦ |
ዳዊት የዐሞናውያን አምላክ ከሆነው ሚልኮም ተብሎ ከሚጠራው ጣዖት ራስ ላይ ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በውስጡም የከበረ ዕንቊ ያለበትን ዘውድ ወስዶ በራሱ ላይ ደፋው፤ እንዲሁም ከከተማይቱ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤
ከባዕዳን ሴቶች ጋር የተጋቡ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮጼዴቅ ልጆች ከሆኑት ከኢያሱና ከወንድሞቹ ጐሣ የተገኙ፤ ማዕሤያ፥ ኤሊዔዘር፥ ያሪብና ገዳልያ፤
የኢዮጼዴቅ ልጅ ኢያሱም ከወገኖቹ ካህናትና የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልም ከዘመዶቹ ጋር በመተባበር የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንደገና ሠሩ፤ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ ቻሉ።
እናንተ የጽዮን ቈነጃጅት! ንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ኑ፤ እርሱ እጅግ በተደሰተበት በሠርጉ ቀን እናቱ በራሱ ላይ የደፋችለትን ዘውድ ጭኖአል።
በራሱም ላይ ጥምጥም አደረገለት፤ በጥምጥሙም ላይ ከፊት ለፊት በኩል እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በወርቅ አጊጦ የተሠራውን የቅድስና ምልክት የሆነውን አክሊል አኖረ።
ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ስድስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ እግዚአብሔር በነቢዩ አማካይነት በሐጌ ተናገረ የተናገረውም የይሁዳ ገዢ ለነበረው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ለነበረው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ ነው።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የይሁዳ ገዢ የሆነውን የሰላትያልን ልጅ ዘሩባቤልን፥ ሊቀ ካህናቱን የኢዮሴዴቅን ልጅ ኢያሱንና ተርፈው ከስደት የተመለሱትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ አነሣሣ፤ እነርሱም የአምላካቸውን የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመሩ።
አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ! በርታ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ! በርታ፤ የሀገሪቱ ሕዝብ ሆይ! በርቱ! እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ። እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሊቀ ካህናቱን ኢያሱን በእግዚአብሔር መልአክ ፊት ቆሞ በራእይ አሳየኝ፤ ሰይጣንም ኢያሱን ለመክሰስ በስተቀኙ ቆሞ ነበር።
መልአኩም አገልጋዮቹን “ንጹሕ ጥምጥም በራሱ ላይ አድርጉለት!” ብሎ አዘዘ፤ እነርሱም እንደ ታዘዙት አደረጉ፤ የእግዚአብሔር መልአክ እዚያው ቆሞ እንዳለ አገልጋዮቹ ኢያሱን አዲስ ልብስ አለበሱት።
ዘውዱም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሔሌም ለተባለ ለሔልዳይ፥ ለጦቢያ፥ ለይዳዕያና ለሰፎንያስ ልጅ ሔን ለኢዮስያስ ክብር መታሰቢያ ሆኖ ይቀመጣል።”
አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።
እነሆ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ቀስት ይዞ ነበር፤ አክሊልም ተሰጠው፤ እርሱም ድል ነሺ ሆኖ ከድል ወደ ድል ለመሄድ ወጣ።