ዘካርያስ 14:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሁከትና ፍርሀት ስለሚለቅባቸው እያንዳንዱ ሰው በአጠገቡ ያለውን ሌላ ሰው ይዞ አደጋ ይጥልበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ በሰዎች ላይ ታላቅ ሽብር ይወርዳል፤ እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ አንዱም ሌላውን ይወጋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር የመጣ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ያድራል፤ እርስ በእርሳቸውም ይያያዛሉ፥ አንዱም በሌላው ላይ ይነሣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፣ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፥ እጁም በባልንጀራው እጅ ላይ ይነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ታላቅ ሽብር በእነርሱ ላይ ይሆናል፥ እያንዳንዱም የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፥ እጁም በባልንጀራው እጅ ላይ ይነሣል። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔም ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖር ለማንም ሰው ርኅራኄ አላደርግም፤ እኔ ራሴ እያንዳንዱን ሰው ለጐረቤቱና ለንጉሡ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱ ምድሪቱን ያጠፋሉ፤ እኔም ከእነርሱ እጅ አልታደጋቸውም።”
በዚያን ጊዜ ፈረሶቻቸውን በፍርሃት አስጨንቃለሁ፤ ፈረሰኞችንም አሳብዳለሁ፤ የጠላቶቻቸውን ፈረሶች አሳውራለሁ፤ የይሁዳን ሕዝብ ግን በዐይኔ እየተመለከትኩ እጠብቃቸዋለሁ።
የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ለመከላከል ይዋጋሉ፤ በዙሪያዋም ያሉትን መንግሥታት ሀብት ሁሉ ማርከው ይወስዳሉ፤ ከሚወስዱትም ምርኮ ወርቅ፥ ብርና የልብስ ዐይነት እጅግ ብዙ ይሆናል።
ሦስት መቶው የጌዴዎን ሰዎች እምቢልታቸውን በሚነፉበት ጊዜ እግዚአብሔር እያንዳንዱን የጠላት ወታደር በጓደኛው ላይና በሠራዊቱ ላይ ሰይፉን እንዲያነሣ አደረገ፤ ሠራዊቱም ፊታቸውን ወደ ጽሬራ በመመለስ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፎ በጣባት አጠገብ እስካለው አቤልመሖላ ድረስ ሸሽተው ሄዱ።