ዘካርያስ 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሌዊ ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥ የሺምዒ ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥ በየወገናቸው ሆነው ያለቅሳሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌዊ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የሰሜኢ ቤት ነገድ ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ |
ሺምዒም በዕድሜአቸው ተራ ያሐት፥ ዚዛ፥ ይዑሽና በሪያ ተብለው የሚጠሩ አራት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ያሖት የመጀመሪያው፥ ዚዛ ሁለተኛው ነበሩ፤ ይዑሽና በሪያ ብዙ ልጆች ስላልነበሩአቸው እንደ አንድ ጐሣ ይቈጠሩ ነበር።
ፈዳያም ዘሩባቤልና ሺምዒ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዘሩባቤልም መሹላምና ሐናንያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ሰሎሚት ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ነበሩት።
ሺምዒ፥ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልወለዱም፤ ስለዚህም የስምዖን ነገድ የይሁዳን ነገድ ያኽል አልበዛም።
በምድሪቱ ላይ የእያንዳንዱ ወገን ቤተሰብ ለየራሱ ያለቅሳል፤ ሚስቶቻቸውም ለየራሳቸው ያለቅሳሉ፤ በዚህ ዐይነት የዳዊት ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥ የናታን ቤተሰብ ከነሚስቶቻቸው፥