ቲቶ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ጐልማሶች ራሳቸውን በመቈጣጠር እንዲኖሩ ምከራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ወጣት ወንዶች ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጐልማሶችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲቈጣጠሩ ምከራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጎበዞችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጎበዞችም እንዲሁ ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው። |
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ በኋላ መንፈሴን በሰው ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልምን ያልማሉ፤ ወጣቶቻችሁም ራእይ ያያሉ።
እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ታዘዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።