ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም
ሮሜ 6:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ በዚያን ጊዜ ምን ጥቅም አገኛችሁ? አሁን ከሚያሳፍራችሁ ነገር በቀር ምንም ጥቅም አላገኛችሁም፤ የዚህም ነገር መጨረሻ ሞት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ጥቅም አገኛችሁ? የዚያ ነገር ውጤት ሞት ነው! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ አሁን ከምታፍሩበት ነገር ሌላ ያንጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያን ጊዜ ሥራችሁም እነሆ፥ ዛሬ ታፍሩበታላችሁ፤ መጨረሻው ሞት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ዛሬ ከምታፍሩበት ነገር ያን ጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የዚህ ነገር መጨረሻው ሞት ነውና። |
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም
“አምላኬ ሆይ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ስለ ሆነና በደላችንም ወደ ሰማይ ስለ ደረሰ ፊቴን ወደ አምላኬ ወደ አንተ ለማቅናት ዐፍራለሁ እፈራለሁም።
እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
“ጌታ ሆይ! እኔ ለምንም የማልጠቅም ከንቱ ሰው ነኝ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አፌን በእጄ ይዤ ዝም ከማለት በስተቀር፥ ለአንተ የምሰጠው መልስ የለኝም።
የበልጉም ሆነ የክረምት ዝናብ ሊቀር የቻለው በዚህ ምክንያት ነው፤ አንቺ ዐይነ ዐፋርነትን አስወግደሽ እንደ አመንዝራ ሴት ኀፍረተቢስ ሆነሻል።
ከአንተ ርቀን ብንሄድም እንኳ አሁን ንስሓ ገብተናል፤ በዕፍረትና በጸጸት ራሳችንን ዝቅ አድርገን ደረታችንን እንመታለን፤ በወጣትነት ዘመናችን ለፈጸምነው ኃጢአት ራሳችንን እንወቅሳለን።’
ሕዝቤ ሆይ! ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር ስታደርጉ ጥቂት ኀፍረት ተሰምቶአችሁ ነበርን? ኀፍረት ሊሰማችሁ ቀርቶ ዐይናችሁ እንኳ ሰበር አላለም፤ ስለዚህ ሌሎች እንደ ወደቁ እናንተም ትወድቃላችሁ፤ እኔ በምቀጣችሁ ጊዜ ፍጻሜአችሁ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ባደረጉት ነገር ሁሉ የሚያፍሩ ከሆነ ስለ ቤተ መቅደሱ አሠራር ንድፍ፥ ስለ አደረጃጀቱ ስለ መውጫዎቹና ስለ መግቢያዎቹ፥ ስለ አጠቃላይ፥ አሠራሩ ሁኔታ፥ ስለ ሥነ ሥርዓቱ፥ ስለ ሕጎቹ ሁሉ አስረዳቸው፤ አጠቃላይ ንድፉን አጥንተው ሥርዓቱን ሁሉ ተግባራዊ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ፊት ጻፈው።
ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ ይህን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ማድረግ ብቻም ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ሰዎች ያበረታታሉ።
በአንድ ሰው ምክንያት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአት ምክንያትም ሞት መጣ፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ኃጢአትን ስለ ሠራ ሞት በሰው ሁሉ ላይ መጣ፤
ለአንድ ሰው አገልጋዮች ሆናችሁ ለመታዘዝ ራሳችሁን ስታቀርቡ ለዚያ ለምትታዘዙለት ሰው አገልጋዮች መሆናችሁን ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም ለኃጢአት ብትታዘዙ ሞትን ለሚያመጣባችሁ ኃጢአት አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ ለእግዚአብሔር ብትታዘዙ ግን ጽድቅን ታገኛላችሁ።
ከኃጢአት የሚገኘው ዋጋ ሞት ነው፤ ከእግዚአብሔር የሚሰጠው ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሚገኘው የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ስውርና አሳፋሪ የሆነውን ነገር አስወግደናል፤ በተንኰልም አንሠራም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንለውጥም፤ ይልቅስ እውነትን በይፋ እናሳያለን፤ ራሳችንንም ለሰው ሁሉ ኅሊና በእግዚአብሔር ፊት ግልጥ እናደርጋለን።
ይህ ሐዘናችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑ እንዴት ያለ የመከላከያ መልስ መስጠትን፥ እንዴት ያለ ቶሎ መቈጣትን፥ እንዴት ያለ ፍርሀትን፥ እንዴት ያለ ናፍቆትን፥ እንዴት ያለ ቅናትን፥ እንዴት ያለ ቅጣትንም እንዳስከተለ ልብ ብላችሁ አስተውሉ። እናንተ ደግሞ በሁሉም ነገር ከጉዳዩ ነጻ መሆናችሁን አስመስክራችኋል።
ሆኖም በዚህ ሁኔታ በሞት መቀጣት የሚገባው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በእርሱ ላይ ከመሰከሩበት በኋላ ነው፤ ምስክሩ አንድ ብቻ ከሆነ ግን ያ ሰው አይገደል።
የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገር ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ ሐሳባቸውም የሚያተኲረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው፤ ስለዚህ የእነርሱ መጨረሻ ጥፋት ነው።
ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!
ፍርድ የሚጀመርበት ጊዜ ቀርቦአል፤ ፍርዱ የሚጀመረውም በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ነው፤ ታዲያ፥ ፍርድ የሚጀመረው በእኛ ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?