ሮሜ 14:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንታነጽበትን ነገር እንከተል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችንም የምንተናነጽበትን ማንኛውንም ጥረት እናድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ የሰላም ነገርና እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን ነገር እንከተል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ወንድማችን ይታነጽ ዘንድ ሰላምን እንከተላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲያስ ሰላም የሚቆምበትን እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን እንከተል። |
“ጨው መልካም ነው፤ ይሁን እንጂ፥ የጨውነቱን ጣዕም ካጣ በምን ታጣፍጡታላችሁ? “በእናንተም የፍቅር ጨው ጣዕም ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ ተስማምታችሁ በሰላም ኑሩ፤” አለ።
እኔ ሁሉም እንዲድኑ የሌሎችን ጥቅም እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ ሰውን ሁሉ በማደርገው ነገር ሁሉ እንደማስደስት እናንተም እንዲሁ አድርጉ።
ወንድሞች ሆይ! እንግዲህ ምን ማድረግ ይገባል? ለጸሎት በምትሰበሰቡበት ጊዜ ከእናንተ አንዱ የመዘመር ስጦታ አለው፤ ሌላው የማስተማር ስጦታ አለው፤ አንዱ ስውር የሆነውን ነገር የመግለጥ ስጦታ አለው፤ አንዱ በተለያዩ ቋንቋዎች የመናገር ስጦታ አለው፤ ሌላው የመተርጐም ስጦታ አለው። ታዲያ፥ ይህ ሁሉ ስጦታ ክርስቲያኖችን የሚያንጽ መሆን አለበት።
ሁላችሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ይበልጥ የምወደው ግን ትንቢትን ብትናገሩ ነው፤ ማኅበረ ምእመናን እንዲታነጽ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የሚተረጒም ከሌለ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገር ሰው ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ሰው ይበልጣል።
ክርስቲያን ያልሆነ ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ፤ በዚህ ጊዜ ግን ክርስቲያን የሆነው ወገን ባልም ሆነ ሚስት በምንም ዐይነት ግዴታ አይያዝም። እግዚአብሔር የጠራን በሰላም እንድንኖር ነው።
ሁላችሁም እስከ አሁን የምታስቡት እኛ በእናንተ ፊት ስለ ራሳችን እንደምንከላከል አድርጋችሁ ነውን? እኛ በክርስቶስ ሆነን የምንናገረው በእግዚአብሔር ፊት ነው፤ ወዳጆቼ ሆይ! እኛ ይህን ሁሉ የምንናገረው እናንተን ለማነጽ ብለን ነው።
በተረፈውስ ወንድሞቼ ሆይ! ደኅና ሁኑ! አኗኗራችሁን አስተካክሉ፤ ምክሬን ተከተሉ፤ እርስ በእርሳችሁ ተስማሙ፤ በሰላምም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
ወደ ተረትና መጨረሻ ወደሌለው ወደ ትውልዶች ቈጠራ እንዳይመለሱ እዘዛቸው፤ እነዚህ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉ እንጂ በእምነት ለሚደረገው ለእግዚአብሔር ሥራ አይጠቅሙም።