ራእይ 21:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ክብር ታበራ ነበር፤ የብርሃንዋም ድምቀት እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ፥ እንደ ብርሌ የጠራ የእያሰጲድ ዕንቊ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም በእግዚአብሔር ክብር ታበራ ነበር፤ የብርሃኗም ድምቀት እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ፣ እንደ መስተዋት የጠራ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርም ክብር ነበረባት፥ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ድንጋይ እንደ ኢያሰጲድ ድንጋይ፥ እንደ ብርሌ የጠራ ነበረ፤ |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር መላውን ከተማና በእዚያም በሚሰበሰቡበት ሁሉ ላይ በቀን ጥቅጥቅ ያለ ደመናን፥ በየሌሊቱም በሚንበለበለው የእሳት ብርሃን ይልካል። የእግዚአብሔርም ክብር ከተማይቱን እንደ ትልቅ ድንኳን ሸፍኖ ይጠብቃታል።
በመግዛትና በመሸጥ ተግባር ትጣደፍ ነበር፤ ይህም ሁሉ ወደ ግፍ ሥራና ወደ ኃጢአት መራህ፤ በዚህም ምክንያት የተቀደሰውን ተራራዬን ለቀህ እንድትወጣ አስገደድኩህ፤ ከነዚያ ከሚያብረቀርቁ የከበሩ ድንጋዮች መካከል ጠባቂው ኪሩብ እያባረረ አስወጣህ።
እዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ እየተገለጠ ነበር፤ ድምፁም እንደ ኀይለኛ የውሃ ማዕበል ነበር፤ የክብሩ ነጸብራቅም በምድር ላይ አበራ።
በአራቱም አቅጣጫ ያሉት የከተማይቱ የቅጽር ግንቦች ጠቅላላ ርዝመት ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ከአሁን በኋላ የከተማይቱ መጠሪያ ስም “እግዚአብሔር በዚያ አለ!” የሚል ይሆናል።
ቤተ መቅደሱም ከእግዚአብሔር ክብርና ኀይል የተነሣ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላእክት የያዙአቸው ሰባት መቅሠፍቶች እስከ ተፈጸሙ ድረስ ማንም ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት አልቻለም።
ከእንግዲህ ወዲህ ሌሊት አይኖርም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።
በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያሰጲድንና የሰርዲኖን ዕንቊ ይመስል ነበር፤ በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቊ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበረ፤
በዙፋኑ ፊት ጥርት ያለ የሚያንጸባርቅ የመስተዋት ባሕር ነበረ፤ በመካከል፥ በዙፋኑ ዙሪያ በስተፊትና በስተኋላ ብዙ ዐይኖች ያሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።