ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።
ራእይ 13:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለተኛው አውሬ ለመጀመሪያው አውሬ ምስል የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን ተሰጠው፤ የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠውም ምስሉ ለመናገር እንዲችልና ለእርሱ የማይሰግዱት ሁሉ እንዲገደሉ ያደርግ ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም የመጀመሪያው አውሬ ምስል መናገር እንዲችል ለምስሉ እስትንፋስ ለመስጠትና ለዚህም ምስል የማይሰግዱ ሁሉ እንዲገደሉ ለማድረግ ሥልጣን ተሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአውሬው ምስል እንዲናገርም ሆነ ለአውሬው ምስል የማይሰግዱትን እንዲያስወግዳቸው ለአውሬው ምስል እስትንፋስ እንዲሰጠው ተፈቀደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአውሬው ምስል ሊናገር እንኳ ለአውሬውም ምስል የማይሰግዱለትን ሁሉ ሊያስገድላቸው፥ ለአውሬው ምስል ትንፋሽ እንዲሰጠው ተሰጠው። |
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።
እንደነዚህ ያሉት ምስሎች በዱባ ተክል ውስጥ ለወፍ ማስፈራሪያ እንደሚተከሉ ነገሮች ናቸው፤ መናገር አይችሉም፤ መራመድ ስለማይችሉ ሰዎች ይሸከሙአቸዋል፤ ጒዳት ማድረስም ሆነ ጥቅም ማስገኘት ስለማይችሉ፥ ፈጽሞ አትፍሩአቸው።”
ደግሞም በዚህ አውሬ ራስ ላይ ስለ ነበሩት ዐሥር ቀንዶችና በኋላ ስለ በቀለው ትንሽ ቀንድ፥ እንዲሁም ለትንሹ ቀንድ ቦታ ለመተው ተነቃቅለው ስለ ወደቁት ሦስት ቀንዶች ለማወቅ ፈለግኹ። ይህ ትንሽ ቀንድ ዐይኖችና አፍ ነበረው፤ ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ አስፈሪ ሆኖ በትዕቢት ይናገር ነበር።
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
ከእንጨት ተጠርቦ የተሠራውን ነገር “ንቃ!” ከድንጋይ ተቀርጾ የተሠራውንም ነገር “ተነሥ!” ለምትል ለአንተ ወዮልህ! ለመሆኑ ጣዖት አንዳች ምሥጢር ሊገልጥልህ ይችላልን? እነሆ ጣዖት በብርና በወርቅ ተለብጦ የተሠራ ነው፤ የሕይወት እስትንፋስ ግን ፈጽሞ የለውም።
ከዚህ በኋላ አንድ አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ የስድብ ስሞች ነበሩ።
የመጀመሪያውን አውሬ ተክቶ በእርሱ ሥልጣን ይሠራ ነበር፤ ምድርና በእርስዋ ላይ የሚኖሩት ሁሉ ለመጀመሪያው አውሬው እንዲሰግዱ አደረገ፤ ይህም አውሬ ያ ለሞት የሚያደርስ ቊስል የዳነለት የመጀመሪያው አውሬ ነው።
በመጀመሪያው አውሬ ፊት እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተአምራት ምክንያት በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር፤ በሰይፍ ቈስሎ ለዳነው ለአውሬው ክብር ምስል እንዲሠሩም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዛቸዋል።
እነርሱን ከሚያሠቃየው እሳት የሚወጣው ጢስ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት ያደረጉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”
ሌላ ሦስተኛ መልአክም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ፥ ምልክቱን በግንባራቸው ወይም በእጃቸው የሚያደርጉ ሁሉ፥
የመጀመሪያው መልአክ ሄደና ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬው ምልክት ባለባቸውና ለአውሬው ምስል በሚሰግዱ ሰዎች ላይ መጥፎና የሚያሠቃይ ቊስል ወጣባቸው።
እነርሱ በበጉ ላይ ጦርነት ይከፍታሉ፤ ነገር ግን በጉ የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ ድል ይነሣቸዋል፤ ከእርሱ ጋር ያሉት የተጠሩ የተመረጡና የታመኑ ናቸው።”
ዕቅዱን እንዲፈጽሙ ይህን ሐሳብ በልባቸው ያኖረ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም እነርሱ በአንድ ሐሳብ ይስማማሉ፤ የመንገሥ ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ያስረክባሉ።
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
ከዚህ በኋላ ዙፋኖችን አየሁ፤ በዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው አየሁ፤ ስለ ኢየሱስ በመመስከራቸውና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሶች አየሁ፤ እነርሱ ለአውሬውና ለምስሉ ያልሰገዱ፥ ምልክቱንም በግንባራቸውም ሆነ በእጃቸው ላይ ያላደረጉ ናቸው፤ እነርሱ ከሞት ተነሥተው ከክርስቶስ ጋር ሺህ ዓመት ነገሡ።