ምሳሌ 29:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌባ ጋር የሚተባበር ራሱን የጠላ ሰው ነው፤ ቢምልም እንኳ እውነትን አይናገርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌባ ግብረ አበር የገዛ ራሱ ጠላት ነው፤ የመሐላውን ርግማን እየሰማ ጭጭ ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሌባ ጋር የሚካፈል ነፍሱን ይጠላል፥ መርገምን ይሰማል፥ ነገር ግን ምንም አይገልጥም። |
መሪዎችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ግብረ አበሮች ሆኑ፤ እያንዳንዱ ሁልጊዜ ገጸ በረከትና ጉቦ ይቀበላል፤ አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች መብት አይጠብቁም፤ ባሎቻቸው የሞቱባቸውንም ሴቶች አቤቱታ አይሰሙም።
እርሱም አንድ ቀን እናቱን እንዲህ አላት፤ “አንድ ሰው አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር በሰረቀሽ ጊዜ ያን የሰረቀሽን ሰው ስትረግሚው ሰምቼሽ ነበር፤ እነሆ ያ ብር በእኔ እጅ ነው፤ እርሱንም የወሰድኩ እኔ ነበርኩ።” እናቱም “ልጄ! እግዚአብሔር ይባርክህ!” አለችው።
ዮናታንም “ይህንንስ ከአንተ ያርቀው! አትሞትም፤ ትልቅም ሆነ ትንሽ አባቴ ከእኔ የሚሰውረው ነገር የለም፤ ይህንንም ነገር ቢሆን አባቴ ከእኔ አይሰውርም በፍጹም አይደረግም!” አለው።