ዐይንህ ብዥ ብዥ ስለሚልብህ አዳዲስ ነገሮችን የምታይ ይመስልሃል፤ በትክክል ማሰብም ሆነ መናገር አትችልም።
ዐይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤ አእምሮህም ይቀባዥራል።
ዐይኖችህ ልዩ ነገሮችን ያያሉ፥ ልብህም ጠማማ ነገርን ይናገራል።
ዐይኖችህ ጋለሞታዎችን ያያሉ፥ ያንጊዜም አፍህ ጠማማ ነገርን ይናገራል።
በአደባባይ የሚቀመጡት ያሙኛል። ሰካራሞች በዘፈን ይሰድቡኛል።
ጥበብ ከክፉ ሰዎች መንገድና ከጠማማ ንግግራቸው ያድንሃል።
ወይን ጠጅ ፌዘኛ፥ ጠንካራ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋሉ፤ በእነርሱ ሱስ የተጠመደ ጥበበኛ ሊሆን አይችልም።
በባሕር ውስጥ ያለህና ማዕበል ከሚያንገላታት መርከብ ምሰሶ ላይ የተወዳጀህ ይመስልሃል።
እነርሱ ጠጥተው ሲሰክሩ ሕግን ይረሳሉ፤ የተቸገሩትንም ሰዎች መብት ችላ ይላሉ።
እየጠጡም ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ አማልክትንም አመሰገኑ።
በንጉሣቸው ክብረ በዓል ቀን መኳንንቱ ብዙ የወይን ጠጅ በመጠጣት ሰክረው ታመሙ፤ ጋጋሪውም ለሚያፌዙ ሰዎች ምልክት ለመስጠት እጁን ዘረጋ።