“ለአሕዛብ ሕዝቦች የተሸጡ አይሁድ ወገኖቻችንን ራሳችን ልንቤዣቸው በማሰብ የሚቻለንን ሁሉ አደረግን፤ እናንተ ደግሞ እነሆ፥ የገዛ ወንድሞቻችሁ የሆኑት አይሁድን ወገኖቻቸው ለሆናችሁት ለእናንተ ባርያዎች አድርገው ራሳቸውን እንዲሸጡላችሁ በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ!” ብዬ ገሠጽኳቸው፤ መሪዎቹም የሚመልሱት ቃል አጥተው ዝም አሉ።
ዘሌዋውያን 25:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምናልባት በመካከልህ የሚኖር አንድ መጻተኛ ባለጸጋ ሲሆን፥ እስራኤላዊ ወገንህ ደኽይቶ ለዚያ መጻተኛ ወይም ከእርሱ ቤተሰብ ለአንዱ ራሱን በባርነት ያስገዛ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆንና ከወገናችሁ አንዱ ደኽይቶ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ ወይም ከመጻተኛው ወገን ለአንዱ ራሱን ቢሸጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም በአንተ ዘንድ ለተቀመጠው እንግዳ ወይም ለመጻተኛው የቤተሰብ አባላት ቢሸጥ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው፥ ወይም ለእንግዳው ወይም ለወገኖቹ ዘር ቢሸጥ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው ወይም ለእንግዳው ወይም ለወገኖቹ ዘር ቢሸጥ፥ |
“ለአሕዛብ ሕዝቦች የተሸጡ አይሁድ ወገኖቻችንን ራሳችን ልንቤዣቸው በማሰብ የሚቻለንን ሁሉ አደረግን፤ እናንተ ደግሞ እነሆ፥ የገዛ ወንድሞቻችሁ የሆኑት አይሁድን ወገኖቻቸው ለሆናችሁት ለእናንተ ባርያዎች አድርገው ራሳቸውን እንዲሸጡላችሁ በማድረግ ላይ ትገኛላችሁ!” ብዬ ገሠጽኳቸው፤ መሪዎቹም የሚመልሱት ቃል አጥተው ዝም አሉ።
እነርሱንም በውርስ ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አገልጋዮቻችሁ ይሆናሉ፤ ከእስራኤላውያን ወገኖቻችሁ መካከል ግን ማንንም በማስጨነቅ አትግዙ።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?