ዘሌዋውያን 25:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በመካከላችሁ የሚኖሩትን የመጻተኞችን ልጆች መግዛት ትችላላችሁ፤ በምድራችሁ የተወለዱትም እንደነዚህ ያሉት ልጆች የራሳችሁ ንብረት መሆን ይችላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም በመካከላችሁ ከሚኖሩት መጻተኞችና ከተወለዱት ወገናቸው ባሪያዎችን ግዙ፤ ንብረታችሁም ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው ከእናንተ ጋር ካሉት ከቤተሰቦቻቸው ውስጥ ባርያዎችን ትገዛላችሁ፤ ርስትም ይሆኑላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት ስደተኞች ልጆች ለራሳችሁ ትገዛላችሁ፤ ከዘመዶቻቸውም በምድራችሁ የሚኖሩት ሁሉ ለርስታችሁ ይሁኑአችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት መጻተኞች፥ በምድራችሁም ውስጥ ከወለዱአቸው በእናንተ መካከል ከሚቀመጡት ከዘራቸው ውስጥ ባሪያዎችን ግዙ፤ ርስትም ይሁኑላችሁ። |
እነርሱንም በውርስ ለልጆቻችሁ ማስተላለፍ ትችላላችሁ፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ አገልጋዮቻችሁ ይሆናሉ፤ ከእስራኤላውያን ወገኖቻችሁ መካከል ግን ማንንም በማስጨነቅ አትግዙ።