ነገር ግን ለመዋጀት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ባይኖረው ርስቱ እስከ ተከታዩ የኢዩቤልዩ ዓመት ድረስ በዚያው በገዛው ሰው እጅ ሊቆይለት ይችላል። በዚያም ዓመት ርስቱ ለባለቤቱ ይመለሳል።
ዘሌዋውያን 25:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በዓመቱ ውስጥ መልሶ መዋጀት ባይችል፥ መልሶ የመዋጀት መብቱን ያጣል፤ ቤቱም ለገዛው ሰው ወይም ለዘሮቹ ቀዋሚ ንብረት ሆኖ ይቀራል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት እንኳ ለሻጩ አይመለስለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሉው ዓመት ከማለቁ በፊት መዋጀት ካልቻለ ግን፣ ቅጥር በተሠራለት ከተማ ውስጥ ያለው ቤት የገዢውና የልጅ ልጆቹ ንብረት ሆኖ ይቀራል፤ በኢዮቤልዩ አይመለስለትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ዓመትም እስከሚፈጸም ባለው ጊዜ ሁሉ ባይቤዠው፥ ቅጥር ባለው ከተማ ውስጥ ያለው ቤት ለገዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘለዓለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩም ከእርሱ ነፃ አይወጣም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ዓመት እስኪጨረስ ባይቤዠው ቤቱ ለገዡ ይሆናል፤ ቅጥር ባለበት ከተማ ያለውን ያን ቤት ይመረምሩለታል፤ ለገዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘለዓለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩ ዓመትም አይወስዱበትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ዓመትም እስኪጨረስ ባይቤዠው፥ ቅጥር ባለበት ከተማ የሚሆን ቤት ለገዛው ለልጅ ልጁ ለዘላለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩም ከእርሱ አይወጣም። |
ነገር ግን ለመዋጀት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ባይኖረው ርስቱ እስከ ተከታዩ የኢዩቤልዩ ዓመት ድረስ በዚያው በገዛው ሰው እጅ ሊቆይለት ይችላል። በዚያም ዓመት ርስቱ ለባለቤቱ ይመለሳል።
ቅጽር ባልተሠራላቸው መንደሮች ውስጥ የሚገኙ ቤቶችን መሸጥ የሚችሉት ግን የእርሻ መሬቶች በሚሸጡበት ዐይነት ይሆናል፤ ባለ ንብረቱ እንደገና የመዋጀት መብት አለው፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ንብረቱን መመለስ አለበት።