በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።
ዘሌዋውያን 25:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ዘር ካልዘራንና ሰብል ካልሰበሰብን ምን እንበላለን ብላችሁ ብትጠይቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም፣ “ካልዘራን ወይም ሰብላችንን ካልሰበሰብን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን?” በማለት ትጠይቁ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን እናንተ፦ ‘ካልዘራን፥ እህላችንንም ካላከማቸን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን?’ ብትሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም፦ ‘ካልዘራን፥ እህላችንንም ካላከማቸን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን?’ ብትሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም፦ ካልዘራን፥ እህላችንንም ካላከማቸን በሰባተኛው ዓመት ምን እንበላለን? ብትሉ፥ |
በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።
አሜስያስ፥ ነቢዩን “አስቀድሜ የከፈልኩትስ ያ ሁሉ ገንዘብ እንዴት ሊሆን ነው?” ሲል ጠየቀው። ነቢዩም “እግዚአብሔር ከዚህ ገንዘብ ይበልጥ የበዛ ሊሰጥህ ይችላል!” ሲል መለሰለት።
ሰባተኛው ዓመት ግን ለእኔ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሆኖ ምድሪቱ ፍጹም ዕረፍት የምታደርግበት ጊዜ ነው። በዚህ ዓመት ዘርህን አትዘራም፤ የወይን ተክልህንም አትገርዝም።
በምድር ሰንበት ዓመት የሚበቅለው ሰብል ሁሉ ለአንተ፥ ለወንድ አገልጋይህ፥ ለሴት አገልጋይህ፥ ለቅጥረኛህ፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ጊዜያዊ መጻተኛ ምግብ ይሆናል።
ከእስራኤላውያን ጋር የሚጓዙ የውጪ አገር ሰዎች ሥጋ ለመብላት የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነበር፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ማልቀስ ጀመሩ፦ “የምንበላውን ሥጋ ከየት እናገኛለን!
እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።