ዘሌዋውያን 19:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ፍርድ አታዛቡ፤ ለድኻው አታድላለት፤ ለትልቁም ሰው ልዩ አክብሮት አትስጥ፤ ለብርቱው አታድላ፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ፍርድን ፈጽሞ አታጓድሉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በጽድቅ ፍረድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በፍርድ ዐመፃ አታድርጉ፤ ለድሃ አታድላ፤ ባለጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍርድ ዓመፃ አታድርጉ፤ ለድሀ አታድላ፥ ባለ ጠጋውንም አታክብር፤ ነገር ግን ለባልንጀራህ በእውነት ፍረድ። |
በተጨማሪ ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መርጠህ በሕዝቡ ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የኀምሳ አለቆችና የዐሥር አለቆች አድርገህ ሹም። እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፥ እምነት የሚጣልባቸውና በጉቦም የማይደለሉ ሰዎች መሆን አለባቸው።
በዚህ ጊዜ ጳውሎስ ሐናንያን፥ “አንተ በኖራ የተለሰነ ግድግዳን የምትመስል! አንተንም እግዚአብሔር ይመታሃል! በሕግ መሠረት የእኔን ጉዳይ ልትፈርድ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እንዲመቱኝ ታዛለህን?”
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’
እግዚአብሔር አምላካችሁ ከባዕዳን አማልክት ሁሉና ከኀይላትም ሁሉ በላይ ታላቅና ብርቱ ስለ ሆነ በፍርሃት መከበር ይገባዋል። እርሱ በፍርድ አያዳላም፤ ጉቦም አይቀበልም።
“ ‘መብት በመግፈፍ መጻተኞችን፥ ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆችንና ባሎቻቸው የሞቱባቸው መበለቶችን የሚያንገላታ ሁሉ የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይበሉ።