“ሴት የወር አበባ በምታይበት ጊዜ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ትሆናለች፤ እርስዋንም የሚነካ ማንም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።
ዘሌዋውያን 15:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የወር አበባ በማየት ላይ ስላለች ሴት ወይም ወንድም ሆነ ሴት ፈሳሽ ነገር ከሰውነታቸው በሚወጣ ጊዜ ወይም ካልነጻች ሴት ጋር ስለሚተኛ ወንድ የተሰጠ መመሪያ ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት፣ ፈሳሽ ነገር የሚወጣቸውን ወንድ ወይም ሴት፣ በሥርዐቱ መሠረት ርኩስ ከሆነች ሴት ጋራ የሚተኛውን ወንድ በሚመለከት ሕጉ ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በወር አበባዋም ለታመመች፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ የረከሰችንም ሴት ለሚገናኝ ሰው ሕጉ ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግዳጅዋም ደም ለሚፈስሳት፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ ከረከሰችም ሴት ጋር ለሚተኛ ሰው ሕጉ ይህ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመርገምዋም ለታመመች፥ ፈሳሽም ነገር ላለባቸው ለወንድም ለሴትም፥ የረከሰችንም ሴት ለሚገናኝ ሰው ሕጉ ይኸው ነው። |
“ሴት የወር አበባ በምታይበት ጊዜ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ርኩስ ትሆናለች፤ እርስዋንም የሚነካ ማንም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል።