ዘሌዋውያን 14:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሻጋታው ምልክት በራሱ ቤት ውስጥ መኖሩን የተገነዘበ ማንም ሰው ሄዶ ለካህኑ ‘በቤቴ ሻጋታ መሰል ነገር አለ’ ብሎ ይንገር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለቤቱ ወደ ካህኑ ሄዶ፣ ‘በቤቴ ውስጥ ተላላፊ በሽታ የሚመስል ነገር አይቻለሁ’ ብሎ ይንገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤቱ ባለቤት መጥቶ ካህኑን፦ ‘ደዌ የሚመስል ነገር በቤቴ ውስጥ ያለ ይመስለኛል’ ብሎ ይንገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባለቤቱ መጥቶ ካህኑን፦ ‘ደዌ በቤቴ ውስጥ እንዳለ አይቻለሁ’ ብሎ ይንገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለቤቱ መጥቶ ካህኑን፦ ደዌ በቤቴ ውስጥ እንዳለ ይመስለኛል ብሎ ይንገረው። |
ካህኑም ሄዶ የሻጋታውን ዐይነት ከመመርመሩ በፊት በቤቱ ውስጥ ያለው ዕቃ ሁሉ እንዲወጣ ትእዛዝ ይስጥ፤ አለበለዚያ በቤቱ ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ካህኑ ወደ ቤት ገብቶ ይመርምር፤
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ‘ይህን ርግማን እልካለሁ፤ ወደ እያንዳንዱ ሌባና በስሜ ምሎ በሐሰት ወደሚናገር ሰው ቤት ይገባል፤ በገባበትም ጊዜ በዚያ ቈይቶ ቤታቸውን ሁሉ ያፈራርሰዋል’ ይላል።”
እነዚህንም የረከሱ ጣዖቶች ወደ ቤትህ አታስገባ፤ ብታስገባ ግን አንተም እንደ እነርሱ ትጠፋለህ፤ እነርሱ ለጥፋት የተገቡ ስለ ሆነ በጣም ልትጠላቸውና ልትጸየፋቸው ይገባል።
ካገኘነው ዕቃ መካከል ውብ የሆነ የባቢሎናውያን ካባ፥ ሁለት ኪሎ ያኽል የሚመዝን ብርና ግማሽ ኪሎ ያህል የሚመዝን ምዝምዝ ወርቅ አየሁ፤ እነርሱንም ለማግኘት ብርቱ ፍላጎት ስላደረብኝ ወስጃቸዋለሁ፤ እነርሱንም ብሩ ከታች ሆኖ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተቀብረዋል።”