La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 13:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያ ሰው ቊስሉን ሳይሆን በቊስሉ ዙሪያ ያለውን ጠጒር ይላጭ፤ ካህኑም እንደገና በሚያሳክከው በሽታ ምክንያት ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከቈሰለው ቦታ በቀር ጠጕሩን ይላጭ፤ ካህኑ ሰባት ተጨማሪ ቀን ሰውየውን ያግልል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይላጫል፥ ቈረቈሩ ግን አይላጭም፤ አሁንም ካህኑ ቈረቈር ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ይለየዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቈረ​ቈሩ ግን አይ​ላ​ጭም፤ ካህ​ኑም ቈር​ቈር ያለ​በ​ትን ሰው ሰባት ቀን ደግሞ ይለ​የ​ዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቈረቈሩ ግን አይላጭም፤ ካህኑም ቈረቈር ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ደግሞ ይዘጋበታል።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 13:33
4 Referencias Cruzadas  

ካህኑ ቊስሉን ይመርምር፤ በዙሪያው ካለው የሰውነት ቆዳ ይልቅ ወደ ውስጥ ጐድጒዶ በእርሱ ላይ የበቀለውም ጠጒር ወደ ቢጫነት በመለወጥ ስስ ሆኖ ከተገኘ የራስ ወይም የአገጭ ቈረቈር ወይም የሥጋ ደዌ ስለ ሆነ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ።


በሰባተኛው ቀን እንደገና ካህኑ ይመርምረው፤ ቊስሉ እየተስፋፋ ካልሄደ፥ ወደ ቢጫነት የተለወጠ ጠጒርም ከሌለና በዙሪያው ካለው ከሌላው ሰውነቱ ቆዳ ይልቅ ጐድጒዶ ካልተገኘ፥


በሰባተኛውም ቀን እንደገና ካህኑ ቊስሉን ይመርምር፤ ቊስሉ በመስፋፋት ላይ ካልተገኘና በዙሪያውም ካለው የሰውነቱ ቆዳ ይልቅ የጐደጐደ ካልሆነ ያ ሰው የነጻ መሆኑን ያስታውቅለት፤ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል።


ነገር ግን ቊስሉ ነጭ ሆኖ በዙሪያው ካለው ቆዳ ይልቅ ጐድጐድ ብሎ ባይገኝና ጠጒሩም ወደ ነጭነት ባይለወጥ፥ ካህኑ ያን ሰው ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ፤