ሰቈቃወ 3:64 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክ ሆይ! ለፈጸሙት ተግባር የሚገባቸውን ዋጋ ስጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ እጆቻቸው ላደረጉት፣ የሚገባውን መልሰህ ክፈላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ትከፍላቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ክፈላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታው። አቤቱ፥ እንደ እጃቸው ሥራ ፍዳቸውን ትከፍላቸዋለህ። |
እኔም እንዲህ በማለት ጸለይኩ፦ “የሠራዊት አምላክ ሆይ! የሰውን ልብና አእምሮ የምትመረምር አንተ ቅን ፈራጅ ነህ፤ እነሆ ችግሬን ለአንተ አስታወቅሁ፤ ስለዚህም በእነዚህ ሕዝብ ላይ የምትፈጽመውን በቀል እንዳይ አድርገኝ።”
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እባክህ አስታውሰኝ፤ እርዳኝም፤ አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ፤ ከትዕግሥትህ ብዛት የተነሣ እንድጠፋ አታድርገኝ፤ ይህም ስድብ የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቀስት መደገን የሚችሉትን ቀስተኞች በባቢሎን ላይ ይዘምቱ ዘንድ ጥሩአቸው፤ ከተማይቱን ይክበቡ፤ ማንም እንዳያመልጥ ተጠባበቁ፤ የክፉ ሥራዋንም ዋጋ ክፈሉአት፤ በሌሎች ላይ የፈጸመችውንም ግፍ በእርስዋም ላይ ፈጽሙባት፤ እርስዋ በእስራኤል ቅዱስ በእኔ ላይ ተዳፍራለች፤
አጥፊዎች በባቢሎን ላይ ስለ ዘመቱ ወታደሮችዋ ተማረኩ፤ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እኔ ለሁሉም እንደየሥራው ዋጋውን የምከፍል አምላክ ስለ ሆንኩ፥ ባቢሎን በፈጸመችው ግፍ መጠን ፍዳዋን እከፍላታለሁ።
ከባቢሎን ሽሹ! ሕይወታችሁንም ለማትረፍ አምልጡ! ባቢሎን በሠራችው ኃጢአት ምክንያት በከንቱ አትለቁ! እኔ ለእርስዋ የሚገባትን ቅጣት በመስጠት የምበቀልበት ጊዜ ነው።
በሰጠችው መጠን ስጥዋት፤ ባደረገችውም ሥራ እጥፍ ክፈልዋት፤ እርስዋ ልዩ ልዩ መጠጦችን በቀላቀለችበት ጽዋ ውስጥ እጥፍ ኀይለኛ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤
እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።