ሰቈቃወ 3:59 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በእኔ ላይ የደረሰውን በደል ሁሉ አይተሃልና ፍትሕን ስጠኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኔ ላይ የተደረገውን ግፍ አየህ፤ ፍርዴን ፍረድልኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፥ ፍርዴን ፍረድልኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፤ ፍርዴን ፍረድልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ጭንቀቴን አይተሃል፥ ፍርዴን ፍረድልኝ። |
አባቴ ይስሐቅ የሚያመልከው የአብርሃም አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን በሰደድከኝ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር መከራዬንና ልፋቴን አይቶ ባለፈው ሌሊት ገሥጾሃል።”
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምን ወለድሽኝ? ዕድል ፈንታዬ ከአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ጋር መከራከርና መነታረክ ሆኗል፤ እኔ ገንዘብ ለማንም አላበደርኩም ወይም ከማንም አልተበደርኩም፤ ሆኖም ሰው ሁሉ ይረግመኛል።