መሳፍንት 9:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይራ ዛፍም ‘ለአማልክትና ለሰዎች ጠቃሚ የሆነውን ዘይቴን መስጠት ትቼ በዛፎች ላይ ልንገሥን?’ አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የወይራ ዛፍም፣ ‘ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፣ እግዚአብሔርና ሰዎች የሚከበሩበትን ዘይቴን መስጠት ልተውን?’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወይራ ዛፍም፥ “ከዛፎች በላይ ለመወዛወዝ ስል፥ እግዚአብሔርና ሰዎች የሚከበሩበትን ዘይቴን መስጠት ልተውን?” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይራዋ ግን፦ እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያከብርበትን ቅባቴን ትቼ በዛፎች ላይ ለመንገሥ ልሂድን? አለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይራው ግን፦ እግዚአብሔርና ሰዎች በእኔ የሚከበሩበትን ቅባቴን ትቼ በዛፎች ላይ እንድሰፍፍ ልሂድ? አላቸው። |
እርሾ ያልነካው ምርጥ የሆነ የስንዴ ዱቄት ወስደህ የወይራ ዘይት በመጨመር ቂጣ አዘጋጅ፤ እንዲሁም ዘይት ያልገባበት ሌላ ቂጣ አዘጋጅ፤ ሌላ ስስ ቂጣም ጋግረህ ዘይት ቀባው፤
“ደግሞም እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እንደ ቀባውና ኀይልም እንደ ሰጠው ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ እርሱን መልካም ነገርን እያደረገና በዲያብሎስ የተያዙትን ሁሉ እየፈወሰ ተዘዋወረ።
“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤