ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!”
መሳፍንት 9:57 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እግዚአብሔር የሴኬም ሰዎች ስለ ክፋታቸው ዋጋ የሆነውን መከራ እንዲቀበሉ አደረገ፤ በዚህ አኳኋን የጌዴዎን ልጅ ኢዮአታም በረገማቸው ጊዜ በእነርሱ ላይ እንደሚደርስባቸው የተናገረው ሁሉ ተፈጸመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰው፤ የይሩባኣል ልጅ የኢዮአታም ርግማን ደረሰባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ሁኔታ እግዚአብሔር የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰው፤ የይሩበኣል ልጅ የኢዮአታም ርግማን ደረሰባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የሰቂማን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፤ የይሩበኣል ልጅ የኢዮአታምም ርግማን ደረሰባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የሴኬምን ሰዎች ክፋት ሁሉ በራሳቸው ላይ መለሰባቸው፥ የይሩበኣል ልጅ የኢዮአታም እርግማን ደረሰባቸው። |
ምንም እንኳ እኔ እግዚአብሔር መርጦ የሾመኝ ንጉሥ ብሆን ዛሬ ደካማነት ተሰምቶኛል፤ እነዚህ የጸሩያ ልጆች በእኔ ላይ እጅግ የበረቱ ዐመፀኞች ሆነውብኛል፤ እነዚህን ነፍሰ ገዳዮች እግዚአብሔር ራሱ የሚገባቸውን ቅጣት ይስጣቸው!”
በአክዓብ ዘመነ መንግሥት ሒኤል ተብሎ የሚጠራ የቤትኤል ተወላጅ ኢያሪኮን መልሶ ሠራ፤ እግዚአብሔር በነዌ ልጅ በኢያሱ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው ቃል መሠረት ሒኤል የኢያሪኮን የመሠረት ድንጋይ በሚያኖርበት ጊዜ የበኲር ልጁ አቢራም ሞተበት፤ የቅጽርዋንም በሮች በሚሠራበት ጊዜ ታናሹ ልጁ ሠጉብ ሞተ።
አባቴ ዳዊት ሳያውቅ ኢዮአብ ስለ ገደላቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ደም እግዚአብሔር ኢዮአብን ይቀጣዋል፤ ኢዮአብ ከእርሱ የተሻሉትን ሁለት ንጹሓን ሰዎች ገድሎአል፤ እነርሱም የእስራኤል ጦር አዛዥ አበኔርና የይሁዳ ጦር አዛዥ ዐማሣ ነበሩ።
በዚያን ጊዜ ኢያሱ፦ “ይህቺን የኢያሪኮን ከተማ ለመገንባት የሚነሣ የተረገመ ይሁን፤ መሠረቱን ሲጥል የበኲር ልጁ ይጥፋ፤ መዝጊያውን ሲያቆም የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ፤” ብሎ ረገመ።
አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።
አቤሜሌክ ከሞተ በኋላ የዶዶ የልጅ ልጅ የፑአ ልጅ ቶላዕ እስራኤልን ለማዳን ተነሣ፤ እርሱም ከይሳኮር ነገድ ሲሆን የሚኖረውም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ሻሚር ተብላ በምትጠራ ስፍራ ነበር፤
ይህ ካልሆነ ግን ከአቤሜሌክ እሳት ወጥቶ የሴኬምንና የቤትሚሎንን ሰዎች ይብላ፤ እንዲሁም ከሴኬምና ከቤትሚሎ እሳት ወጥቶ አቤሜሌክን ይብላ።”
ይህም የሆነው ወንድማቸው አቤሜሌክ የገደላቸውን የጌዴዎንን ሰባ ልጆች ደምና እነርሱንም እንዲገድል ያበረታቱትን የሴኬምን ሰዎች ለመበቀል ነው።