መሳፍንት 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፥ በሲናው አምላክ ፊት፥ ተራራዎች ተናወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣ በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል አምላክ ከጌታ ፊት፥ በሲናው ጌታ ፊት ተራሮች ቀለጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮች ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ ተነዋወጡ፤ ያም ሲና ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተራሮች ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ ቀለጡ፥ ያም ሲና ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ። |
እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት መላው የሲና ተራራ በጢስ ተሞላ። ጢሱም ከእሳት ምድጃ እንደሚወጣ ዐይነት ሆኖ ወደ አየር ተትጐለጐለ፤ ሰዎቹም እጅግ ፈርተው ተንቀጠቀጡ።
ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤
በእግዚአብሔር ፊት ተራራዎች ይንቀጠቀጣሉ፤ ኰረብቶችም ይቀልጣሉ፤ በእግዚአብሔር ፊት ምድር ትናወጣለች፤ ዓለምና በውስጥዋ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ።
ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ የዝናብም ጐርፍ ምድርን እየጠራረገ አለፈ፤ ውቅያኖስ ከፍተኛ ድምፅ አሰማ፤ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ።