መሳፍንት 5:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዲቦራ ሆይ! ንቂ! ንቂ! ንቂ! መዝሙርም ዘምሪ! የአቢኒዔም ልጅ ባራቅ ሆይ! ተነሣ! ምርኮህንም እየመራህ ወደ ፊት ገሥግሥ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘ዲቦራ ሆይ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ንቂ፤ ቅኔም ተቀኚ፤ የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ሆይ፤ ተነሣ፤ ምርኮኞችህንም ማርከህ ውሰድ’ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባራቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሺ፥ ዲቦራ ሆይ፦ ተነሺ፤ አእላፍን ከሕዝብ ጋር አስነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቅኔውንም ተቀኚ፤ ባርቅ ሆይ! በኀይል ተነሣ፤ ዲቦራም ባርቅን አጽኚው፥ የአቢኒሔም ልጅ ባርቅም ሆይ! ምርኮህን ማርክ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንቂ፥ ንቂ፥ ዲቦራ ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቅኔውን ተቀኚ፥ ባርቅ ሆይ፥ ተነሣ፥ የአቢኒኤም ልጅ ሆይ፥ ምርኮህን ማርክ። |
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ወደ ላይ ወደ መኖሪያህ በወጣህ ጊዜ ምርኮን ይዘህ ሄድክ፤ ከዐመፀኞች እንኳ ሳይቀር ከሰዎች ሁሉ ምርኮን ተቀበልክ።
የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።
እግዚአብሔር ሆይ! ተነሥ፤ ተነሥተህ ኀይልህን ግለጽ! በጥንት ዘመን በነበረው ትውልድ መካከል እንዳደረግኸው ተነሥ፤ ረዓብ የተባለውን የባሕር ዘንዶ ቈራርጠህ ያደቀቅከው አንተ ነህ።
ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።