መሳፍንት 17:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚካም “ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም “እኔ በይሁዳ ግዛት ከምትገኘው ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምኖርበትን ስፍራ እየፈለግሁ ነው” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሚካም፣ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተ ልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚካም፥ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚካም፥ “ከወዴት መጣህ?” አለው። እርሱም፥ “ከይሁዳ ቤተ ልሔም የሆንሁ ሌዋዊ ነኝ፤ የምቀመጥበትንም ስፍራ ለመሻት እሄዳለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚካም፦ ከወዴት መጣህ? አለው። እርሱም፦ ከቤተ ልሔም ይሁዳ የሆንሁ ሌዋዊ ነኝ፥ የምቀመጥበትንም ስፍራ ለመሻት እሄዳለሁ አለው። |
ይህም ሰው የሚኖርበትን ስፍራ ለማግኘት ከቤተልሔም ተነሥቶ ሄደ፤ በጒዞም ላይ ሳለ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ወደሚገኘው ወደ ሚካ ቤት መጣ፤