መሳፍንት 16:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሶምሶን ከሴቲቱ ጋር ተኝቶ የቈየው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ከዚያን በኋላ ከመኝታው ተነሣ፤ የከተማይቱን ቅጽር በር፥ ሁለቱን ምሶሶዎችና መቈለፊያዎቹን ሁሉ ፈነቃቀለ፤ ያንን ሁሉ በትከሻው ተሸክሞ ከኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኮረብታ ድረስ ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ሳምሶን እዚያ የተኛው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ተነሥቶም የከተማዪቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቹ ጋራ መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር በሙሉ ነቅሎ በትከሻው ላይ ካደረገ በኋላ፣ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኰረብታ ጫፍ ድረስ ተሸክሞት ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሳምሶን እዚያ የተኛው እስከ እኩለ ሌሊት ብቻ ነበር፤ ተነሥቶም የከተማይቱን ቅጥር በር ከሁለት መቃኖቸ ጋር መወርወሪያውንና ማያያዣውን ጭምር በሙሉ ነቅሎ በትከሻው ላይ ካደረገ በኋላ፥ በኬብሮን ፊት ለፊት እስካለው ኰረብታ ጫፍ ድረስ ተሸክሞት ወጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፤ በእኩለ ሌሊትም ተነሥቶ የከተማዪቱን በር መዝጊያ ያዘ፤ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያው ጋር ነቀለው፤ በትከሻውም ላይ አደረገ፤ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ፤ በዚያም ጣለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሶምሶንም እስከ እኩለ ሌሊት ተኛ፥ እኩለ ሌሊትም በሆነ ጊዜ ተነሥቶ የከተማይቱን በር መዝጊያ ያዘ፥ ከሁለቱ መቃኖችና ከመወርወሪያውም ጋር ነቀለው፥ በትከሻውም ላይ አደረገ፥ በኬብሮንም ፊት ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ተሸክሞት ወጣ በዚያም ጣለው። |
መንገዱን በርግዶ በሚከፍትላቸው መሪ አማካይነት በተከፈተው ሰፊ በር ተግተልትለው ይወጣሉ፤ እግዚአብሔርም ንጉሣቸው በፊታቸው እየሄደ ይመራቸዋል።
የጋዛም ሰዎች ሶምሶን በዚያ መኖሩን ሰምተው ያንን ቦታ በመክበብ በከተማይቱ በር ሌሊቱን ሙሉ ሲጠብቁት ዐደሩ፤ “እስኪነጋ ጠብቀን እንገድለዋለን” ብለው በማሰብ ሌሊቱን ሙሉ አደፈጡ፤