መሳፍንት 11:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮፍታሔም የገልዓድን ሽማግሌዎች፦ “እንግዲህ ወደ ቤት ከመለሳችሁኝ በኋላ እግዚአብሔር በዐሞናውያን ላይ ድልን በሚያጐናጽፈኝ ጊዜ እኔ የእናንተ መሪ እሆናለሁ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮፍታሔም የገለዓድን ሽማግሌዎች፣ “አሞናውያንን ለመውጋት ወደ አገሬ ብትመልሱኝና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ቢሰጣቸው በርግጥ አለቃችሁ እሆናለሁ?” ሲል ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮፍታሔም፥ “አሞናውያንን ለመውጋት ወደ አገሬ ብትመልሱኝና ጌታ በእጄ አሳልፎ ቢሰጣቸው በእርግጥ አለቃችሁ እሆናለሁ?” ሲል ጠየቃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮፍታሔም የገለዓድን ሽማግሌዎች፥ “ከአሞን ልጆች ጋር ለመዋጋት ብትወስዱኝ፥ እግዚአብሔርም በእጄ አሳልፎ ቢሰጣቸው፥ እኔ አለቃችሁ እሆናለሁን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮፍታሔም የገለዓድን ሽማግሌዎች፦ ከአሞን ልጆች ጋር ለመዋጋት ወደ አገሬ ብትመልሱኝ፥ እግዚአብሔርም በእጄ አሳልፎ ቢሰጣቸው፥ እኔ አለቃችሁ እሆናለሁን? አላቸው። |
እነርሱም ዮፍታሔን “አሁን እኛ ወደ አንተ ተመልሰናል፤ ከእኛ ጋር ዘምተህ ዐሞናውያንን እንድትወጋልንና የገለዓድ ሕዝብ ሁሉ መሪ እንድትሆን እንፈልጋለን” አሉት።