ነገር ግን የይሁዳ ሕዝብ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ማባረር አልቻሉም፤ ስለዚህም ኢያቡሳውያን እስከ አሁን ድረስ በኢየሩሳሌም ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ይኖራሉ።
መሳፍንት 1:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን በጦርነት ያዙአት፤ ሕዝብዋንም በሰይፍ ፈጁ፤ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው ያዟት፤ ከተማዪቱንም በሰይፍ ስለት መተው፣ በእሳት አቃጠሏት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወግተው ያዟት፤ ከተማይቱንም በሰይፍ ስለት መተው፥ በእሳት አቃጠሏት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም ልጆች ኢየሩሳሌምን ተዋግተው ያዙአት፤ በሰይፍ ስለትም መቱአት፤ ከተማዪቱንም በእሳት አቃጠሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም ልጆች ኢየሩሳሌምን ተዋግተው ያዙአት፥ በሰይፍ ስለትም መቱአት፥ ከተማይቱንም በእሳት አቃጠሉአት። |
ነገር ግን የይሁዳ ሕዝብ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ማባረር አልቻሉም፤ ስለዚህም ኢያቡሳውያን እስከ አሁን ድረስ በኢየሩሳሌም ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ይኖራሉ።
የብንያም ነገድ ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን አላስወጡም ነበር፤ ከዚያን ጊዜም ጀምሮ ኢያቡሳውያን ከብንያም ሕዝብ ጋር እስከ ዛሬ ድረስ አብረው መኖርን ቀጠሉ።