ይህም ንጉሣዊ ትእዛዝ አዳር ተብሎ የሚጠራው ዐሥራ ሁለተኛ ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን፥ ማለትም አይሁድ እንዲገደሉ በታቀደበት ዕለት በመላው የፋርስ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሁሉ ሥራ ላይ እንዲውል ተወሰነ።
መሳፍንት 1:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዶኒቤዜቅም ከፊታቸው ሸሸ፤ እነርሱ ግን አባረው ከያዙት በኋላ የእጆቹንና የእግሮቹን አውራ ጣቶች ቈረጡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አዶኒቤዜቅም ከዚያ ሸሸ፤ እነርሱ ግን አሳድደው ያዙት፤ የእጆቹንና የእግሮቹንም አውራ ጣቶች ቈረጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አዶኒቤዜቅም ሸሸ፤ እነርሱ ግን አሳደው ያዙት፤ የእጆቹንና የእግሮቹንም አውራ ጣቶች ቈረጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዶኒቤዜቅም ሸሸ፤ ተከታትለውም ያዙት፤ የእጁንና የእግሩንም አውራ ጣቶች ቈረጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዶኒቤዜቅም ሸሸ፥ አሳድደውም ያዙት፥ የእጁንና የእግሩንም አውራ ጣት ቈረጡ። |
ይህም ንጉሣዊ ትእዛዝ አዳር ተብሎ የሚጠራው ዐሥራ ሁለተኛ ወር በገባ በዐሥራ ሦስተኛው ቀን፥ ማለትም አይሁድ እንዲገደሉ በታቀደበት ዕለት በመላው የፋርስ የንጉሠ ነገሥት ግዛት ሁሉ ሥራ ላይ እንዲውል ተወሰነ።
እርሱንም ዕረድና ከደሙ ጥቂት ወስደህ የአሮንንና የልጆቹን ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ትቀባለህ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ርጨው።
እነሆ እኔ እግዚአብሔር እናንተንም የምላችሁ ይህ ነው፦ ‘አልታዘዛችሁም፤ ወገኖቻችሁ ለሆኑ እስራኤላውያንም ነጻነት አልሰጣችሁም፤’ ስለዚህም እኔ በጦርነት፥ በራብና በወረርሽኝ ትሞቱ ዘንድ እተዋችኋለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገውም ነገር የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲሠቀቅ አደርጋለሁ።
በከተማይቱ ዙሪያ በማቅራራት ደንፉ! እነሆ ባቢሎን እጅዋን ሰጥታለች፤ ግንቦችዋ ተጥሰዋል፤ ቅጽሮችዋም ፈራርሰዋል፤ ባቢሎናውያንን እበቀላለሁ፤ እናንተም ተበቀሉአቸው፤ በሌሎች ላይ የፈጸሙትን ጭካኔ በእነርሱም ላይ ፈጽሙባቸው፤
አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።