ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ኢዮብ 7:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተስፋ ቈርጬአለሁ፤ መኖርም አልፈልግም፤ የሕይወቴም ዘመን አጭር ስለ ሆነ ተወኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወቴን እጸየፋለሁ፤ ዘላለም መኖር አልፈልግም፤ ዘመኔ እንደ እስትንፋስ ነውና ተወኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥ ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንድታገሥ ለዘለዓለም እኖራለሁን? ሕይወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘላለም ልኖር አልወድድም፥ የሕይወቴ ዘመን እስትንፋስ ነውና ተወኝ። |
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ኤልያስ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓ ተጓዘ፤ ከዚህ በኋላ ጒዞውን ቆም አድርጎ፥ በአንድ የክትክታ ዛፍ ጥላ ሥር ተቀመጠ፤ ሞቱንም በመመኘት “እግዚአብሔር ሆይ! አሁንስ ይብቃኝ፤ ከቀድሞ አባቶቼ አልበልጥምና ነፍሴን ውሰድ!” ሲል ጸለየ።
ተራ ሰዎች እንደ አየር ናቸው፤ በከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሰዎች ተጨባጭነት እንደሌለው ምኞት ናቸው፤ ሁለቱ በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ።
ከመከራ በቀር ያገኘሁባት ጥቅም ባለመኖሩ ሕይወት በእኔ ዘንድ ትርጒም አልተገኘላትም፤ ይህም ከንቱ ስለ ነበር ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ይቈጠራል።
ፀሐይ ከወጣ በኋላ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ ላከ፤ የፀሐዩም ሐሩር ራሱን ስላቃጠለው ዮናስ ተዝለፈለፈ፤ ሞትንም በመመኘት “ከመኖር ይልቅ መሞት ይሻለኛል” አለ።