ኢዮብ 5:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው የተባረከ ነው! ስለዚህ የልዑል እግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን ቻይ አምላክ ተግሣጽ አትናቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፥ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነገር ግን እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፥ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ። |
“የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን።
ደግሞም እነዚያን በትዕግሥት የጸኑትን “የተባረኩ ናቸው” እንላቸዋለን፤ ኢዮብ እንዴት እንደ ታገሠ ሰምታችኋል። ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን መልካም ነገር አይታችኋል፤ በዚህም ጌታ መሐሪና ርኅሩኅ መሆኑን ተመልክታችኋል።