ኢዮብ 5:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ ገና በእኩለ ቀን፥ በሌሊት ጨለማ ውስጥ እንዳሉ ሆነው ይደናበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀን ጨለማ ያገኛቸዋል፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። |
ያካበተው ንብረት ሁሉ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ ይወድማል፤ በሰው እጅ ያልተቀጣጠለ እሳትም ያቃጥለዋል፤ በቤቱ ውስጥ የሚተርፈውን ንብረት ሁሉ ያጋየዋል።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋው፤ በእጅ እስከሚዳሰስ ድረስ ጥቅጥቅ ያለ ጨለማ የግብጽን ምድር ይሸፍናል” አለው።
በዳበሳ እንሄዳለን፤ መንገዳችንንም የምንከታተለው በዳበሳ ነው፤ በድንግዝግዝታ እንዳለን ዐይነት በቀትር እንደናቀፋለን፤ በኀያላን ሰዎችም መካከል እንደ ሞቱ ሰዎች ነን።
በእኩለ ቀን እንደ ዕውር ትደናበራለህ፤ የምትሄድበትንም መንገድ ማግኘት አትችልም፤ የምትሠራውም ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ዘወትር ጭቈናና ምዝበራ ይደርስብሃል፤ የሚረዳህም ሰው አታገኝም።